የብሪታኒያ ምክር ቤት አዲሱን ትውልድ ከትንባሆ የሚያቅብ ሕግ አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሪታኒያ ምክር ቤት አዲሱን ትውልድ ሲጋራ ከመግዛት የሚከለክለውን ከትንባሆ ነጻ ትውልድ ሕገ ደንብ አጸድቋል፡፡
የሀገሪቱ ምክር ቤት ያጸደቀው ይህ ህግ ከፈረንጆች 2008 ወዲህ የተወለዱ ብሪታኒያውያንን ሲጋራ እና ሌሎች የትምባሆ ምርቶችን ከመግዛት የሚከለክል መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ይህ ክልከላ በዓለም ላይ እስካሁን ከነበሩ የፀረ ትንባኦ ርምጃዎች አንጻር ጠንከር ያለ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
ሕጉ ተፈጻሚ ለመሆን የንጉስ ቻርለስ 3ኛን ይፋዊ ይሁንታ ብቻ እንደሚጠብቅ የተነገረ ሲሆን፥ ከመጪው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ጀምሮ በእንግሊዝ፣ ዌልስ፣ ስኮትላንድ እና ሰሜን አየር ላንድ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ዌስ ስትሪቲንግ ሕጉ መጽደቁ ከማጨስ ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን ለማስቆም ትልቅ ርምጃ እንደሆነ መናገራቸውን ኖቪኒቴ ዶት ኮም ዘግቧል፡፡
በአመለወርቅ ደምሰው