ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከስዊዲን አቻቸው ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዎስ (ዶ/ር) ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያ ማልመር ስቴነርጋርድ ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትሮቹ በስዊድን ስቶኮልም ያደረጉት ውይይት በአፍሪካ ቀንድ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።
ጌዲዮን (ዶ/ር) ሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸው በማንሳት ወዳጅነቱን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በንግድና ኢንቨስትመንት ረገድ የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸው÷ የስዊዲን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ማሪያ ማልመር ስቴነርጋርድ በበኩላቸው÷ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን ጠቁመው÷ ስዊዲን በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደምትፈልግ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።