ሊቨርፑል ክሪስታል ፓላስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በሜዳው አንፊልድ ክሪስታል ፓላስን ያስተናገደው ሊቨርፑል 3 ለ 1 አሸንፏል።
ቀን 11 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ አይሳክ፣ ሮበርትሰን እና ቨርትዝ ባስቆጠሯቸው ግቦች ነጥቡን 58 በማድረስ በሊጉ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የክሪስታል ፓላስን ብቸኛ ግብ ሙኖዝ ከመረብ አሳርፏል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ላለመውረድ የሚፋለሙት ቶተንሃም ሆትሰፐር እና ዌስትሃም ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
በሜዳው ኤቨርተንን ያስተናገደው ዌስትሃም ዩናይትድ በቶማስ ሶቼክ እና ካሉም ዊልሰን ግቦች 2 ለ 1 ሲያሸንፉ፤ ቶተንሃም በበኩሉ አስቀድሞ መውረዱን ያረጋገጠውን ዎልቭስ በዦአዎ ፓሊኒሀ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በጨዋታው ቶተንሃም ወሳኙን አጥቂ ዶሚኒክ ሶላንኪን እና አማካዩ ዣቪ ሳይመን በወሳኝ ሰዓት በጉዳት አጥቷል፡፡
ቀደም ሲል በተካሄደ ጨዋታ ፉልሃም አስቶንቪላን 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወቃል።