Fana: At a Speed of Life!

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሞዛምቢክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሞዛምቢክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያ ማኑኤላ ሉቃስ ጋር ተወያይተዋል።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ሁለቱ ሀገራት በፓን አፍሪካኒዝም ዕሳቤ የተቃኘ ልዩ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቅሰው፥ የረጅም ጊዜ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተጨባጭ በሆኑ የትብብር መስኮች መንቀሳቀስ እንደሚገባ አንስተዋል።

ማሪያ ማኑኤላ ሉቃስ በበኩላቸው ሀገራቸው በኢትዮጵያ የልማት ተሞክሮዎች ዙሪያ ልምድ ለመቅሰምና ለመለዋወጥ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ በተለያዩ ዘርፎች አብሮ ለመሥራትና የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ዝግጁ ነን ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.