ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት አቀባበል አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገዋል።
የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ልማትና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጡ የሚችሉ ተጨባጭ ስራዎችን ቅድሚያ የሰጠ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለእውነተኛ አፍሪካዊ አጋርነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡