የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ፕሬዚዳንቱን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀብለናል ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን በማኖር ለመላው ጥቁር ህዝቦች ነጻነት ፋና ወጊ የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
ከንቲባዋ በመልዕክታቸው ፕሬዚዳንቱ የሰው ዘር መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያና የአፍሪካዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ የሰመረ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።