Fana: At a Speed of Life!

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋት የ13 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ተደረገ

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋት የ13 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ተደረገ

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (ኢ- ሞቢሊቲ) ዘርፍ ላይ በስፋት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ዶዳይ የ13 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አግኝቷል፡፡

ድጋፉ ዶዳይ የንግድ ሥራውን እንዲያስፋፋ እና የባትሪ ቅያሬ ማዕከላትን ለመገንባት እንደሚያስችለው ተገልጿል፡፡

የተደረገው የገንዘብ ድጋፍ 8 ሚሊየን ዶላር በካፒታል ሲሆን 5 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ በብድር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ድጋፉን ያደረጉት የእንግሊዝ መንግሥት የልማት ፋይናንስ ተቋም፣ የጃፓን የኢንቨስትመንት ተቋማት እና ናጋሴ  Nagase & Co ናቸው፡፡

ዶዳይ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ከ2 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌቶችን በሀገር ውስጥ በመገጣጠም ለገበያ ማቀረተቡ ተጠቁሟል፡፡

አዲሱ ድጋፍም በሚቀጥሉት 12 ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ ዙሪያ 30 የባትሪ ቅያሬ ጣቢያዎችን ለመገንባትና የተጠቃሚዎችን ቁጥር ወደ 3 ሺህ ለማሳደግ እንደሚውል ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም በሀገሪቱ ያለውን የካርቦን ልቀትን ለመቀነስና ለአካባቢ ጥበቃ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ኢትዮጵያ ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለምታደርገው ሽግግር ትልቅ እመርታ እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.