Fana: At a Speed of Life!

የጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ከፍ ያሉ እመርታዎች የተመዘገበበት አንዱና ዋነኛው መስክ ነው – ዶ/ር መቅደስ ዳባ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በለውጡ ዓመታት የጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ከፍ ያሉ እመርታዎች የተመዘገበበት አንዱና ዋነኛው መስክ ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ።

ሚኒስትሯ ይህንን ያሉት የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች በሚቀርቡበት የምክክር መድረክ ላይ ነው።

መድረኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ሲሆን÷ ዶ/ር መቅደስ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ዓበይት ስኬቶችን በተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል።

ዘርፉ ከለውጡ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት ካስመዘገባቸው ዋና ዋና ስኬቶች መካከል ለ30 ዓመታት የቆየው የጤና ፖሊሲን በመከለስ መከላከል ከሚለው መርህ በተጨማሪ አክሞ የማዳን ቁርጠኛ የፖሊሲ አመራር፣ የተቋም ግንባታ፣ የጤና መሠረተ ልማት ለውጦች፣ መድኃኒት፣ ክትባት እና የህክምና ግብዓቶች ምርት አቅርቦት እና ቁጥጥር ጭማሪ እንዲሁም የጤና ፋይናንስ እመርታ ቁልፍ እና ዋነኞቹ የለውጥ ስራዎች ናቸው ብለዋል።

‎በተለይም የወረርሽኝ ልየታ እና ቁጥጥር፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ፣ የጤና ባለሙያዎችን ማብቃትና ቁጥራቸውን ማሳደግ፤ የዲጂታል ጤና፣ በዘርፉ የተተገበሩ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ኢትዮጵያ በጤና ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ግንባር ቀደም ስኬቶቿ ናቸውም ነው ያሉት።

የጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ከፍ ያሉ እመርታዎች የተመዘገበበት አንዱና ዋነኛው መስክ መሆኑንም አስረድተዋል።

ይህም ኢትዮጵያ በተለያዩ መድረኮች ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተመርጣ ድርድሮችን እና ንግግሮችን እንድትመራ አስችሏታል ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.