Fana: At a Speed of Life!

ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ ብሩህ ተስፋ ነው – ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቻፖ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ ብሩህ ተስፋ ነው አሉ፡፡

በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዚዳንቱ ኢንስቲትዩቱን የጎበኙ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት እያከናወነች ያለችውን መጠነ ሰፊ ስራዎች በተመለከተ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ወቅት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መጻኢውን የዓለም ሁኔታ የሚወስን መሆኑን ገልጸው፥ ሁሉም ሀገራት በትኩረት ሊሰሩበት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በኢንስቲትዩቱ ውስጥ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተሰማርቶ የሚገኘውን ወጣት የሰው ኃይል አድንቀው፥ ይህ የሰለጠነ ወጣት ኃይል ከኢትዮጵያ ባለፈ የአህጉሪቱን የወደፊት የዕድገት አቅጣጫ የሚወስን ነው ብለዋል፡፡

ወጣቱ በፈጠራ ስራ ላይ ተሰማርቶ ማየት ትልቅ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ ተቋሙ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ ብሩህ ተስፋ መሆኑን ገልጸዋል።

አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር፣ በጋራ መስራትና ልምድ መለዋወጥ ለአፍሪካ ፈጣን ዕድገት የጋራ ብልጽግና መሰረት መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.