Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በርካታ ዜጋ ተኮር የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት ዓመታት በመዲናዋ በርካታ ዜጋ ተኮር የልማት ስራዎች ተከናውነዋል አሉ፡፡

የአዲስ አበባን የአምስት ዓመታት የልማት ጉዞ የሚያሳይ አውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ በይፋ ተከፍቷል።

ከንቲባ አዳነች በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ አዲስ አበባን ንፁህ እና ውብ በማድረግ ጤናማ ከተማን ከጤናማ ማሕበረሰብ ጋር በማዋሀድ ከአፍሪካ ቀዳሚ ከተሞች ተርታ ማሰለፍ ተችሏል፡፡

ባለፉት ዓመታት ከተማዋን የሕንጻ ጫካ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ምርታማነትን በግብርናና ኢንዱስትሪ መግለጥ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በከተማ እድገት ዜጋ ተኮር ልማትን ያረጋገጡ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውንም አብራርተዋል፡፡

በአምስቱ የመዲናይቱ በሮች ስድስት ግዙፍ የገበያ ማዕከላት መገንባታቸው ቃል የተገባውን በተግባር የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተዘጋጀው አውደ ርዕይ በሁሉም ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያሳይ ሲሆን ለአምስት ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል፡፡

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.