የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ከኦማኑ ሱልጣን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ከኦማኑ ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪክ አልሰይድ ጋር ተወያይተዋል።
ፖምፒዮ ከኦማኑ ሱልጣን ጋር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በቀጠናው ሰላም፣ መረጋጋትና ልማት ጉዳይ ላይ ስለመምከረራቸው በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰሞኑን በእስራኤል እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል የተመሰረተውን ግንኙነት አስመልክተው በእስራዔል፣ በሱዳን፣ በባህሬን እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት አድርገዋል።
የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ስምምነት አስመልከቶ ኦማን ለተመሰረተው ግንኙነቱ ድጋፏን አስታውቃለች።
የእስራዔል የደህንነት ሚኒስትርም ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በተጨማሪ ባህሬንና ኦማን ቀጣዮቹ አገራት እንደሚሆኑ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ሆኖም ኦማን በጉዳዩ ዙሪያ እስከአሁን ያለችው ነገር የለም።
ምንጭ፦ ሬውተርስ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።