Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ለዓለም አቀፍ ኩነቶች እና ውድድሮች ተመራጭ ሆናለች – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ ለአህጉር እና ዓለም አቀፍ ኩነቶች እና ውድድሮች ተመራጭ ከተማ ሆናለች አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልክት÷ ዛሬ ማለዳ በመዲናዋ የሼህ ዛይድ በጎ አድራጎት 5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በመስቀል አደባባይ መካሄዱን ገልፀዋል፡፡

በውድድሩ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ሯጮች፣ ታዋቂ አትሌቶች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ህጻናት እና የውጭ ሀገራት ዜጎች ተሳታፊ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በአሜሪካ፣ በብራዚል፣ በአቡ ዳቢ፣ በህንድ፣ በቻይና እና በካይሮ ከተሞች ሲካሄድ የነበረውን ይህንን ታላቅ ዓለም አቀፍ ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ማስተናገዷን ጠቅሰዋል፡፡

የሼህ ዛይድ በጎ አድራጎት 5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር አዘጋጆች ውድድሩን ለማካሄድ አዲስ አበባን በመምረጣቸው ምስጋና ያቀረቡት ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ አዲስ አበባ ለአህጉር እና ዓለም አቀፍ ኩነቶች እና ውድድሮች ተመራጭ ከተማ ሆናለች ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.