Fana: At a Speed of Life!

እርዳታ የሚቀበል ሀገር ሉዓላዊ ነኝ ማለት አይችልም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ‎እርዳታ የሚቀበል ሀገር ሉዓላዊ እና ነጻ ነኝ ማለት አይችልም አሉ፡፡

4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተከፍቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በሁሉም መስክ ማምረት ሉዓላዊነትን ያጎናጽፋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ማምረት ካልቻለች የግብርና ምርትና ሂደቱ በሰዎች በጎ ፈቃድ ላይ መውደቁ አይቀርም ነው ያሉት፡፡

ለምግብ ግብዓት የሚሆኑ የማምረቻ መሳሪያዎች፣ ምርጥ ዘሮች እና ማዳበሪያዎችን በሀገር ውስጥ ማምረት የተሟላ የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ አስረድተዋል፡፡

ነዳጅ እና ጋዝ ማምረት ባለመቻላችን ብዙ ፈተና ገጥሞናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያ ብዙ የነዳጅ እና ጋዝ ሀብት እንዳላቸው ሀገራት ከፍተኛ አቅም ቢኖራትም እስካሁን ድረስ ማምረት ባለመቻላችን ተቸግረናል ሲሉም አብራርተዋል፡፡

በሁሉም መስክ ማምረት ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ መሆኑን በማመን ማቀድ፣ መስራት እና መስፋት ይጠበቅብናል ነው ያሉት፡፡

እርዳታ የሚቀበል ሀገር ነጻ እና ሉዓላዊ ነኝ ማለት አይችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያዊያን ልመና በቃን እስካላልን ድረስ ጥገኞች ነን ብለዋል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.