Fana: At a Speed of Life!

በቻይና የርችት ፋብሪካ በተከሰተ ፍንዳታ የ26 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና ሊዩያንግ ከተማ በሚገኝ የርችት ፋብሪካ በተከሰተ ፍንዳታ የ26 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 61 ሰዎች ደግሞ መጎዳታቸው ተሰምቷል።

ከፍንዳታው በኋላ የነፍስ አድን ዘመቻዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ የአካባቢው ባለስልጣናት ከፋብሪካው በ3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ሁሉም ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲለቁ አድርገዋል ነው ተባለው፡፡

ከአደጋው በኋላ በድሮን፣ በአነፍናፊ ውሾች እና ሮቦቶች በመታገዝ 1 ሺህ 500 የነፍስ አድን ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ ሰባት ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስጥ በህይወት ማዳን መቻላቸው ተገልጿል፡፡

የፍንዳታውን መንስኤ እያጣራ የሚገኘው የሊዩያንግ ፖሊስ የፋብሪካውን አመራሮች በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ÷ የተጎዱ ወገኖችን ለማዳን የሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና የአደጋው መንስኤ ተጣርቶ ጥፋተኞች ላይ ህጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ ማሳሰባቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.