Fana: At a Speed of Life!

የህትመት ዘርፍ የለውጡ መንግሥት ትልቅ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ሪፎርም ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ነው – አቶ መሳፍንት ተፈራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የህትመት ዘርፍ የለውጡ መንግሥት ትልቅ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ሪፎርም ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ነው አሉ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ‎‎‎መሳፍንት ተፈራ።

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

‎‎‎‎አቶ መሳፍንት በዚህ ወቅት÷ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያጋጠመውን ተቋማዊ ውስንነቶች በመለየት ተገቢውን ምላሽ መስጠት የሪፎርሙ ተቀዳሚ እርምጃ እንደነበር አመላክተዋል።

የይዘት ጥራትና ብዝኃነትን ማስፋት፣ ሚዲያውን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ ተደራሽነትና ስርጭትን ማሳደግ እንዲሁም ተገቢ አደረጃጀትና መዋቅር መፍጠር የሪፎርሙ ትግበራዎች ዋነኛ ማጠንጠኛዎች ነበሩ ብለዋል።

የለውጡ መንግሥት ስኬቶች ከዘርፉ ባለፈ የሀገሪቱን የወል ትርክት በመቅረጽ አይነተኛ ሚና ተጫውተዋል ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.