Fana: At a Speed of Life!

ሚዲያዎች ለጋራ ማንነትና ለብሔራዊ መግባባት በቁርጠኝነት ሊሠሩ ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሚዲያዎች ለጋራ ማንነትና ለብሔራዊ መግባባት በቁርጠኝነት ሊሠሩ ይገባል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ”የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀውና ባለፉት ዓመታት በሚዲያ ዘርፍና ተቋማት ላይ የተመዘገቡ ስኬቶች በቀረቡበት የምክክር መድረክ ላይ ታድሜ ሀሳቤን አጋርቻለሁ ብለዋል።

‎ባለፉት ስምንት ዓመታት የሚዲያ ምህዳሩን በዲሞክራሲያዊ አውድ ለመዋጀት በተወሰደው ርምጃ ለሀገር ግንባታ የሚረዳ መሠረት መጣሉን ገልጸዋል።

ይህ ውጤት እንዲቀጥልም ሚዲያዎች ከዋልታ ረገጥነትና ከጽንፈኝነት ወጥተው በእውነት ላይ የተመሠረተ ትርክት በመገንባት ለጋራ ማንነትና ለብሔራዊ መግባባት በቁርጠኝነት ሊሠሩ ይገባል ነው ያሉት።

‎ሚዲያዎቻችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በጥናት የታገዘ ጥልቅ ትንተና በማቅረብ፣ ከአርዕስት ሽያጭ ባለፈ ለሀገር አጀንዳዎች ትኩረት መስጠት ይኖርባቸዋል ሲሉም አስገንዝበዋል።

ተግባራቸውም በዓላማ፣ በእይታ፣ በሙያዊ ብቃትና ለሕዝብ ቅርብ በመሆን ላይ ተመስርቶ፣ ሚዛናዊነትን በጠበቀ መልኩ ለሀገር ብልጽግና መንገድ ጠራጊና ችግር ፈቺ ሆነው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.