Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነመራ ቡሊ በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ዓመታት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ገብተዋል አሉ፡፡

በጅማ ከተማ በ3 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነቡ 78 ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል።

አቶ ነመራ ቡሊ በወቅቱ እንዳሉት፤ በክልሉ ባለፉት ዓመታት በትምህርት እና በቴክኖሎጂ ላይ ተጭባጭ ለውጥ ያመጡ ስራዎች ተሰርተዋል።

የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በመንግሥት በጀት እና በሕዝብ ተሳትፎ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባተቻውን አንስተዋል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት በክልሉ ከ20 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን እና የጎጆ ኢንዱስትሪ ሼዶችን በመገንባት ወጣቶችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል።

ክልሉ በተያዘው ዓመት ከ28 ሺህ 800 በላይ ፕሮጀክቶችን በ339 ቢሊየን ብር እያስገነባ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ 260 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው ከ21 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች እንደሚመረቁም አመልክተዋል፡፡

በወርቅአፈራው ያለው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.