የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማከናወን ጀምሯል።
በጉባኤው ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
ምክር ቤቱ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡