Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች ተጠቃሚነትንና ቁልፍ ውሣኔ ሰጪነት እንዲረጋገጥ ሰርተን ተሳክቶልናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት 5 ዓመታት የሴቶች ተጠቃሚነትንና ቁልፍ ውሣኔ ሰጪነት እንዲረጋገጥ ሰርተን ተሳክቶልናል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ እንኳን ለዓለም አቀፍ የእናቶች ቀን አደረሳችሁ ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሴቶች ዛሬ ማልዳችሁ ውቢቷን ቸርችል ጐዳና በመሙላት ለሰጣችሁን ድጋፍ እናመሰግናለን ያሉት ከንቲባዋ÷ ዛሬ በዓለም አቀፍ የእናቶች ቀን መላው የከተማችን ሴቶች የተሳተፉበት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን ዓላማና ግብ የሚደግፍ፣ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል ብለዋል።

ባለፉት 5 ዓመታት በገባነው ቃል መሰረት የሴቶች ተጠቃሚነትንና ቁልፍ ውሣኔ ሰጪነት እንዲረጋገጥ ሰርተን ተሳክቶልናልም ነው ያሉት።

የእናቶችን ጫና ለመቀነስ ልጆቻችሁ ያለምንም ሐሳብ ሁሉም ነገር ተሟልቶላቸው እንዲማሩ ከተማ አስተዳደራችን እጅግ ውጤታማ ስራ ሰርቷል ሲሉም ገልጸዋል።

በአበበች ጎበና የተሰየመ የእናቶችና የህፃናት ሆስፒታል በመገንባት፣ የነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ልህቀት ማዕከል በመገንባት፣ የእንጀራ ፋብሪካዎች ለሴቶች በመገንባት በአጠቃላይ ባለፉት 5 ዓመታት ከፈጠርነው 2 ሚሊየን የሥራ ዕድል 51 በመቶው ሴቶች እንዲሆኑ በመስራት፣ የሴቶችን አይተኬ ሚና እና ክብር የሚወክል አደባባይ በመገንባት እና የመሳሰሉ የሴቶችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ክብር ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ ፍሬ አፍርቷል ሲሉም አብራርተዋል።

አሁንም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በከተማችን ካቀረብናቸው እጩዎች 54 በመቶ ሴቶች ናቸው ያሉት ከንቲባ አዳነች÷ በከተማችን ምክር ቤት ከ40 በመቶ በላይ ሴቶች በመሆናቸው ከዚህ በፊት የነበረውን ተሳትፎ በበለጠ አልቀነዋል ብለዋል።

ይህ ደግሞ ለአጃቢነት ሳይሆን የሴቶች ሚና አይተኬ መሆኑን በማመን ነው በማለት አስገንዝበዋል።

በ7ኛው ምርጫ ብልፅግናን ስትመርጡ፣ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ታስቀጥላላችሁ፤ ሰላማችንም ዘላቂ ሆኖ ይረጋገጣል በማለት ገልጸ÷ የምርጫ ምልክታችን የሥንዴ ነዶ ነው፤ ልክ እንደ ነዶው ተደምረን፤ ማንንም ያልተወ፣ ማንንም ያልዘነጋ አካታች ልማትን እያረጋገጥን እንቀጥላለን ሲሉም አመልክተዋል።

ባለፉት 5 ዓመታት የከተማችንን ሠላም በማረጋገጥ፣ ልማትን በማረጋገጥ አብራችሁን ስለነበራችሁ አዲስ አበባ ከልብ ታመስግናችኋለችም ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.