ዌስትሃም ዩናይትድ ከአርሰናል…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ36ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር የሊጉ መሪ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
አርሰናል 76 ነጥቦችን በመሰብሰብ ሊጉን እየመራ ሲሆን፥ ተጋጣሚው ዌስትሃም ዩናይትድ በበኩሉ 36 ነጥቦችን በመሰብሰብ 18ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጣና ላይ ይገኛል።
የሊጉ መሪ አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ ለማድረግ ወደ ሜዳ ይገባል።
ወራጅ ቀጣና ላይ የሚገኘው ዌስትሃም በበኩሉ÷ በሊጉ ለመቆየት በሚያደርገው ፍልሚያ የዛሬው ጨዋታ እጅጉን ወሳኝ ነው።
ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ በተመሳሳይ ቀን 10 ሰዓት ላይ በርንሌይ ከአስቶንቪላ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከኒውካስል ዩናይትድ እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ከኤቨርተን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።