Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን የተለያየ ልዩነት ቢኖራቸውም በአንድ ሀገር ጥላ ስር የሚኖሩ ወንድማማቾች ናቸው – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህል፣ ቋንቋና የአኗኗር ልዩነት ቢኖራቸውም በአንድ ሀገር ጥላ ስር የሚኖሩ ወንድማማቾች ናቸው አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።

የሁለቱን ክልሎች ሕዝብ ዘመናትን የተሻገር የአብሮነትና የሰላም እሴት የበለጠ ለማጎልበት ያለመ የሕዝብ ለሕዝብ ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት አቶ ኦርዲን በድሪ ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህል፣ ቋንቋና የአኗኗር ልዩነት ቢኖራቸውም በአንድ ሀገር ጥላ ስር የሚኖሩ ወንድማማቾች ናቸው ብለዋል።

በተለይም የሀረርጌ ሕዝቦች በኢትዮጵያ ውስጥ ልዩና ተምሳሌታዊ የሆነ ውህደት እናዳላቸው ጠቅሰው÷ በዋናነትም የሀረሪና የኦሮሞ ሕዝቦች በታሪክ፣ በደምና በላብ የተጋመዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለዚህም ዘመናትን የተሻገረ የሁለቱ ሕዝቦች አብሮነትና ትስስር በማጠናከርና ይህንን ለመሸርሸር የሚደረጉ ጥረቶችን በማክሸፍ ረገድ ኮንፈረንሱ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል።

በመድረኩ ከሀረሪ ክልል ከምስራቅ ዞንና ማያ ከተማ የተውጣጡ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.