ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ተገናኝተን በኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
በውይይቱ ወቅት ለነበራቸው ጠቃሚ የሐሳብ ልውውጥና ቀጣይነት ላለው አጋርነትም ምስጋና አቅርበዋል።