የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ዕጩዎች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2025/26 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ዕጩዎች ይፋ ተደርገዋል፡፡
በዚህም የሊጉ መሪ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ፣ የማንቼስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮለ እና የማቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ በዕጩዎች ውስጥ መካተት ችለዋል።
እንዲሁም የብሬንትፎርድ አሰልጣኝ አንድሪውስ፣ የቦርንማውዝ አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ እና የሰንደርላንዱ አሰልጣኝ ሊ ብሪስ በዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ ተካትተዋል፡፡