የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደብረማርቆስ ከተማ በረራ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያ በረራውን ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ አድርጓል።
በረራ ያደረገው አውሮፕላን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችን በመያዝ ደብረማርቆስ ደርሷል።
እንግዶቹ ደብረማርቆስ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የደብረማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው ለዓመታት የሕዝብ ጥያቄ እንደነበር አሚኮ ዘግቧል፡፡