Fana: At a Speed of Life!

ሰንደርላንድ እና ሊድስ ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሰንደርላንድ እና ሊድስ ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።

አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ የተካሄደው የሰንደርላንድ እና ኤቨርተን ጨዋታ በሰንደርላንድ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

በጨዋታው የሰንደር ላንድ ግቦችን ኢንዞ ለፌ፣ ብራያን ብሮቤይ እና ዊልሰን ኢሲዶር ሲያስቆጥሩ÷ ሜርሊን ሮህል የኤቨርተንን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገው የሊድስ ዩናይትድ እና ብራይተን ጨዋታ በሊድስ 1 ለ 0 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ÷ ዶሚኒክ ካልቨርት ሊዊን የማሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሯል።

እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ብሬንትፎርድ ከክሪስታል ፓላስ 2 ለ 2፤ ወልቭስ ከፉልሃም 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.