በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመምረጥና የመመረጥ መብት የሚረጋገጥበት እኩል የመወዳደሪያ ሜዳ ተፈጥሯል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ሕገ መንግሥታዊ የመምረጥና የመመረጥ መብት የሚረጋገጥበት እኩል የመወዳደሪያ ሜዳ ተፈጥሯል አሉ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ።
ሚኒስትር ዴኤታዋ እንዳሉት÷ በምርጫው ሒደት የሴቶች፣ ወጣቶችና የአካል ጉዳተኞችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማረጋገጥ የሚያስችል ምኅዳር ተፈጥሯል።
በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ለመራጭነት የተመዘገበው ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር የዜጎችን ተሳትፎ በማሳደግ የአሳታፊነት አስቻይ ሁኔታ መፈጠሩን እንደሚያሳይ ገልጸዋል።
የምርጫ ሒደቱን ዴሞክራሲያዊነትና ሰላማዊነት ለማስጠበቅ በተለያዩ አማራጮች ሕዝብን የማንቃትና የማስገንዘብ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ዜጎችም ለሀገር ይበጃል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምፅ በመስጠት የነቃ የፖለቲካ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።