Fana: At a Speed of Life!

የሕብረተሰቡን የመረጃ እውቀት ያሳደገው “የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት” ጉባኤ…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) “የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት” ጉባኤ እንደ ሀገር በመረጃ ልማት የተሰሩ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች በአውደ ርዕይ የቀረቡበት ነበር አሉ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ/ር)።

“የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት” በሚል መሪ ሐሳብ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ ጉባኤ ተጠናቅቋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በጉባኤው ከ30 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች መገኘታቸውን ገልጸው÷ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በአራት ዘርፎች የመረጃ አሰባሰብና ልማት ሥራዎችን ሲከውን መቆየቱን ተናግረዋል።

በዋናነት በሕብረተሰብ ጤና፣ በግብርና ጥናት፣ በቤተሰብ ወጪ ጥናት እና በድርጅት ቆጠራ ሰፊ የመረጃ ልማት ሥራዎች መሰራታቸውን አመልክተዋል።

የመረጃ ልማት ሥራው የሀገር አቀፍ የምርት እድገት ክለሳ ለማድረግ በእጅጉ እንደሚያግዝም ጠቁመዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሃጽዮን በበኩላቸው÷ ጉባኤው ሕብረተሰቡ ስለ መረጃ ያለውን እውቀት ከፍ ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በሔብሮን ዋልታው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.