Fana: At a Speed of Life!

በአካልና በአእምሮ የዳበረ ትውልድ በመገንባት አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋታለን ብለን ስንነሳ በአካልና በአእምሮ የዳበረ ትውልድ መገንባትን ቅድሚያ በመስጠት ነው አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ በቦሌ ክፍለከተማ የተገነቡ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

በይፋ ተመርቀው አገልግሎት መስጠት የጀመሩት መሰረተ ልማቶች አምስት ስፖርት ማዘውተሪያዎችን፣ 95 የህጻናት መጫዎቻዎች፣ ስድስት የህጻናት ማቆያዎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ አንፊ ትያትሮችን ያካተተ ነው፡፡

በተለይም ካፒቴን አበራ ለሚ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በ4ሺህ 900 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የለሚ ኮሚኒቲ ስታዲየምን ገንብተው ማስረከባቸውን ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡

ስታዲየሙ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፣ የመሮጫ ትራክ፣ ጥላ ያለው የተመልካች መቀመጫ፣ ለወጣቶች የስራ እድል የሚውሉ ሱቆች፣ መታጠቢያና መጸዳጃ ቤቶች፣ ጂምናዚየምና የእቃ ማከማቻ መጋዘንንና ያካተተ ነው ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ስታዲየሙን ገንብተው ያስረከቡን ካፒቴን አበራ ለሚ አመስግነው የአካባቢው ነዋሪዎች ስታዲየሙን በእንክብካቤ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.