በኬፕ ታውን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳንላም ኬፕ ታውን የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡
በወንዶች አትሌት መሀመድ ኢሳ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ55 ሴኮንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቋል፡፡
በርቀቱ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ይሁንልኝ አዳነ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን ጨርሷል፡፡
በሴቶች ደግሞ አትሌት ደራ ዲዳ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ18 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት በመግባት 1ኛ በመሆን አጠናቅቃለች፡፡
በርቀቱ የተሳተፉት ሌሎች ኢትየጵያዊያን አትሌቶች መስታወት ፍቅር እና ዋጋነሽ አማረ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን ጨርሰዋል፡፡