Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር የተሻለ ይሰራል ለምንለው ፓርቲ ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል – ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር ይበጃል፤ ለሕዝብም የተሻለ ይሰራል ለምንለው ፓርቲ ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተና አሉ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች።

ወጣት ለምለም ተስፋዬ ሀገርና ሕዝብን በልማት ወደፊት ያራምዳል ለምትለው ፓርቲ ድምጿን ለመስጠት የምርጫውን ቀን እየጠበቀች መሆኑን ተናግራለች።

ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅም የበኩሏን ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን ነው የገለጸችው።

ሌላዋ ወጣት መድኃኒት ተመስገን በበኩሏ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ አንድ ድምጽ ዋጋ እንዳለው ተረድታ ካርዷን በአግባቡ እንደምትጠቀም ተናግራለች።

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የክርክር መድረኮችን መከታተሌ የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ ለመለየት አስችሎኛል ብላለች።

ወጣት እሱባለው መምህሩ እና አማኑኤል አብዮት በሰጡት አስተያየት ምርጫ በቀጣይ ሀገር የሚመራ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በነጻነት የሚመረጥበት መሆኑን አንስተዋል።

ለሀገርና ለሕዝብ የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ ለመለየት እንዲችሉ በመገናኛ ብዙኃንና በተለያየ መንገድ ፓርቲዎች ሲያደርጓቸው የነበሩ ቅስቀሳዎችን ሲከታተሉ እንደነበርም ገልጸዋል።

መራጩ ያወጣውን የምርጫ ካርድ በአግባቡ ሊጠቀምበት እንደሚገባ ወጣቶቹ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ ይበጀናል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የድምጽ መስጫውን ቀን እየተጠባበቁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.