Fana: At a Speed of Life!

በጎማ 2 ምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎማ 2 ምርጫ ክልል ስር በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ ሥርጭት ተጠናቅቋል አለ የምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት።

የምርጫ ክልሉ ጽ/ቤት ኃላፊ ባሻዬ መስፍን ፥ በምርጫ ክልሉ በአጠቃላይ 87 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን እና የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የማጓጓዝ ሥራ መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከቁሳቁስ ሥርጭቱ ጎን ለጎን ደግሞ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ለድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ የሚያስፈልጉ የቦታ ዝግጅት ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በምርጫ ክልሉ ከ108 ሺህ በላይ ዜጎች ድምጽ ለመስጠት የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ነው የገለጹት፡፡

አሁን ላይ በጣቢያዎቹ የምርጫ ቁሳቁስ ገብቶ ለድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ሃላፊው ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.