Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ካራቴ ብሔራዊ ቡድን አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸነፈ

‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2026 የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ካራቴ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያ ቀን ውሎ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን አግኝቷል።

በኬንያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው ውድድር ብሔራዊ ቡድኑ በወንዶች ከ75 ኪሎ ግራም በታች እና ከ53 ኪሎ ግራም በታች እንዲሁም በሴቶች ካታ እና በቡድን ኮሚቴ ባሳየው ድንቅ ብቃት አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸንፏል።

በተጨማሪም በወንዶች ከ67 ኪሎ ግራም በታች እና በቡድን ካታ ውድድር ሁለት የብር ሜዳሊያዎች ተገኝተዋል።

በወንዶች ካታ ከ60 ኪሎ ግራም በታች እና ከ84 ኪሎ ግራም በታች ሶስት የነሐስ ሜዳሊያዎች የተመዘገበባቸው ሌሎች ዘርፎች ናቸው።

በናይሮቢ እየተደረገ ያለው የምስራቅ አፍሪካ የካራቴ ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን አምስት ሀገራት እየተሳተፉ እንደሚገኙ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.