ዴሞክራሲያዊ መብታችንን በመጠቀም ለመምረጥ ተዘጋጅተናል – የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ዴሞክራሲያዊ መብታችንን በመጠቀም ይመራናል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ ነን አሉ፡፡
ነዋሪዎቹ ነገ ግንቦት 24 በሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የመራጭነት ካርድ ከያዙ ቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን የድምጽ መስጫውን ዕለት በጉጉት እየጠበቁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብቶች አንዱ ምርጫ መሆኑን ጠቅሰው÷ በነገው እለት ይመራናል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
በተዘጋጀው የክርክር መድረክ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያቀረቡትን ሀሳብ በንቃት መከታተላቸው ለምርጫ ተሳትፏቸው መልካም ዕድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡
ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልጸዋል።
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያትመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision