ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው በዛሬው ዕለት ከደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል በሚገኘው የሐረጎ መንገድ ላይ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
በአደጋው ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም በርካታ ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ፖሊስ ገልጿል፡፡
የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው በግምት 100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል ውስጥ መግባቱን አሚኮ ዘግቧል፡፡
በሕይወት የተረፉትን ወደ ሕክምና ቦታ ለማድረስ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን፥ የአደጋው ምክንያት በመጣራት ላይ ይገኛል፡፡