Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ እና ኢራን ጦርነት ለማቆም ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም የሚያስችላቸው ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ሀገራቱን እያደራደረች የምትገኘው ፓኪስታን ስምምነቱ በመጪው አርብ በስዊዘርላንድ እንደሚፈረም አስታውቃለች።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስምምነቱ መሰረት የሆርሙዝ ሰርጥ እንደሚከፈት ገልጸው፥ ስምምነቱን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የኢራን ባለስልጣናት ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር የደረሰችበት ስምምነት ለቴህራን ድል ነው ብለዋል።

የስምምነቱ ሙሉ ሃሳብ እስካሁን ይፋ ባይሆንም ከዚህ ቀደም የተደረሰው የተኩስ አቁም እንዲራዘም፣ ተጨማሪ 60 ቀናት ምንም አይነት ጦርነት እንዳይኖርና ሁለቱም ወገኖች ተጨማሪ ንግግሮችን እንዲያደርጉ ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በብርሃኑ አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.