የቢሾፍቱ አቡሴራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ኢትዮጵያን ወደ አቪዬሽን ማዕከልነት የማሸጋገር ሚና…
• አቡሴራ ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከባሕር ጠለል በላይ በ1 ሺህ 910 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ከአዲስ አበባ ቦሌ (2 ሺህ 334 ሜትር) በተሻለ ለአውሮፕላኖች መነሳትና ማረፍ እጅግ ምቹ የአየር ሁኔታን ይሰጣል።
• የአቡሴራ ከፍታ ከአዲስ አበባ ቦሌ ያነሰ በመሆኑ፣ የዓለም አቀፍ በረራ አውሮፕላኖች ሙሉ ነዳጅና ጭነት ይዘው ረጅም ርቀት በቀጥታ እንዲበሩ ሰፊ የአቪዬሽን ምቹነትን ይሰጣል። የአውሮፕላኖች የመጫን አቅምን ጨመረ ማለት ነው።
• ምቹ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ እና የአቪዬሽን ብቃት ደግሞ ሌላኛው ሚናው ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም ካርታ ላይ ያላት ስልታዊ አቀማመጥ (በአውሮፓ፣ በእስያ እና በአፍሪካ መገናኛ መስመር ላይ መገኘቷ) አቡሴራን ለዓለም አቀፍ በረራዎች አጭርና ተመራጭ የመሸጋገሪያ መስመር ያደርገዋል።
• አየውሮፕላን ማረፊያው አራት ዘመናዊ ማኮብኮቢያዎች እና በአንድ ጊዜ እስከ 270 አውሮፕላኖችን ማቆም የሚችል ስፍራም ይኖረዋል። አሁን ካለው የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅም በ4 ነጥብ 4 እጥፍ ይበልጣል።
• የሚገነባው ግዙፍና ዘመናዊ የካርጎ ተርሚናል የዓለም የንግድ ዕቃዎች እና የህክምና አቅርቦቶች ከአምራች ሀገራት ተነስተው ወደ ተጠቃሚዎች የሚሰራጩበት ዋነኛ የአየር ሎጂስቲክስ ማዕከል እንዲሆን ያደርገዋል።
• እንደ አበባ፣ ፍራፍሬ እና ስጋ ያሉ የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት ምርቶች ሳይበላሹ በጥራትና በከፍተኛ ፍጥነት ወደ መላው ዓለም ገበያ እንዲደርሱ ያስችላል። ይህም የዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ማዕከልነታችንን ያረጋግጥልናል ማለት ነው፡፡
• ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኢንደስትሪ ውስጥ እንደ ዱባይ (DXB) እና ሲንጋፖር (Changi) ያሉ ታላላቅ የዓለም መገናኛ ማዕከላት ተርታ ያሰልፋታል።
• ኢትዮጵያን የአፍሪካ ቁልፍ የአቪዬሽን መናኸሪያ በማድረግ ከአህጉራዊ የትራንዚት ማዕከልነት ወደ መላው ዓለም ስልታዊ መገናኛ ድልድይነት ያሸጋግራል፤