ስፔን ሳዑዲ አረቢያን 4 ለ 0 አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የዓለም ዋንጫ በምድብ ስምንት የምትገኘው ስፔን ሳዑዲ አረቢያን 4 ለ 0 አሸነፈች፡፡
ዛሬ ምሽት በተደረገው የምድብ 2ኛ ጨዋታ የስፔንን የድል ግቦች ላሚን ያማል፣ ሚኬል ኦያርዛባል (ሁለት) እና ታማባክቲ (በራሱ መረብ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡
በዚሁ ምድብ የሚገኙት ዩራጋይ እና ኬፕቨርዴ ሌሊት 7 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በምድብ ሰባት ቤልጂየም ከኢራን ምሽት 4 ሰዓት ላይ እንዲሁም ኒውዚላንድ ከግብጽ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡