Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካና ኢራን የሰላም ውይይት በስዊዘርላንድ…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በስዊዘርላንድ የተጀመረው የአሜሪካ እና ኢራን የሰላም ውይይት ከ80 ደቂቃ ንግግር በኋላ መጠናቀቁ ተሰምቷል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የአሜሪካ እና ኢራን የሰላም ውይይት የኳታርና ፓኪስታን አደራዳሪዎች በተገኙበት ነው በዛሬው ዕለት በስዊዘርላንድ የተጀመረው፡፡

የኢራን ተደራዳሪዎች በተደረሰው የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የተጠቀሱ የመግባቢያ ስምምነት ነጥቦች እንዲተገበሩ ግፊት ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡

በተለይም በኢራን እንዳይንቀሳቀሱ በታገዱ ሃብቶች እና በነዳጅ ዘይት ላይ በተጣለው ማዕቀብ ላይ ሃሳብ ልውውጥ መደረጉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ይሁን እንጂ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራንን ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ የሰላም ውይይቱ ከ80 ደቂቃ በኋላ መጠናቀቁ ተመላክቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ለሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ የምታደርገውን ድጋፍ የማታቆም ከሆነ ከባድ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ዝተዋል፡፡

ዛሬ በስዊዘርላንድ ተጀምሮ የነበረው የሁለቱ ሀገራት ድርድር ጦርነቱን በዘላቂነት ማስቆም የሚያስችሉ ነጥቦች ላይ በስፋት ምክክር ይደረጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት ነበር፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.