የማሊ የሽግግር መንግስት መሪ ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አይወዳደርም- ኢኮዋስ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)በማሊ የሚመሰረተው የሽግግር መንግስት መሪ ከሽግግሩ በኋላ በሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለውድድር እንደማይቀርብ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበር(ኢኮዋስ) አስታወቀ።
ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ባውባካር በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣናቸው ከወረዱ በኋላ በስልጣን ላይ ያለው ወታደራዊ መንግስት ስልጣኑን በሲቪል ለሚመራ የሽግግር መንግስት ማስተላለፍ ይገባዋልም ሲሉ የድርጅቱ አባል ሀገራት መሪዎች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የሚመሰረተው የሽግግር መንግስት ለአንድ ዓመት ብቻ በስልጣን ላይ ቆይቶ ምርጫ እንደሚካሔድም ነው ኢኮዋስ ያሳሰበው።
ከዚያም ባለፈ የሽግግሩን መንግስቱን ሊመራ የሚገባው ግለሰብ በእውቀቱ ና በሙያዊ ብቃቱ የሚታወቅ መሆን አለበትም ነው ያለው።
ሆኖም የሽግግር መንግስቱን የመራው ግለሰብ ከአንድ ዓመት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ላይ መሳተፍ እንደማይችል የቀጠናው የኢኮኖሚ ማህበር አባል ሀገራት መሪዎች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።
ማሊን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የነበሩት ኬይታ እና ጠቅላይ ሚስትር ቦውቦ እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣናት ወታደራዊ መንግስቱ ስልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላ መታሰራቸውን በዚህ ሳምንት መለቀቃቸው ይታወሳል።
ምንጭ፡- ሲጂቲኤን
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።