ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም ዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አረጋገጡ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ የኮመንዌልዝና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ኢቬት ኩፐር ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትሮቹ ከለንደን የአየር ንብረት ሳምንት መድረክ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊና የባለብዙ ወገን ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በዚህም በቀጣናዊ ሰላም፣ መረጋጋት፣ ዘላቂ ልማት እንዲሁም በኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።
የአየር ንብረት ተግዳሮቶችን ለመፍታትና የጋራ መፍትሄዎችን ለማምጣት ዓለም አቀፋዊ ጥረቶችን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉዳይ ከሰፊው የዓለም ኢኮኖሚና ልማት ውይይቶች ጋር ማጣጣም አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሶስና አለማየሁ