Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ፡ ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ማከናወኗን አደነቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በስኬት ማከናወኗን ሩሲያ አደነቀች፡፡

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፥ ብልጽግና ፓርቲ 438 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን በማግኘት አሳማኝ ድል ማስመዝገቡን ጠቅሷል፡፡

ሚኒስቴሩ በመግለጫው የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ የምርጫ ታዛቢዎች የምርጫው ሒደት በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ መካሄዱን እንዲሁም ጥሰቶች እንዳልተፈጸሙ መግለጻቸውን አስታውሷል፡፡

ምርጫው በስኬት መጠናቀቁ ኢትዮጵያውያን ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ለሀገሪቱ አስተዳደር ላይ የሚያደርጉትን ድጋፍ አመላካች መሆኑንም የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.