Fana: At a Speed of Life!

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2 ሺህ 882 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 2 ሺህ 882 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ እንዲሁም በዲፕሎማ እና በሌሎች መርሐ ግብሮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው፡፡

የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተሾመ ነቃጥበብ (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ ተመራቂዎች ለዚህ ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የትምህርት፣ እውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከልነቱን ለማጠናከር አዳዲስ ስትራቴጂዎችን እየተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡።

ከቀድሞ በተለየ መልኩ በብዛትና በጥራት የታነጹ “አርአያ መምህራንን” ለማፍራት የተቀናጀ የስልጠና ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ዩኒቨርሲቲው ፕሮግራሞቹን ከሀገሪቱ ወቅታዊ የሥርዓተ ትምህርት ፍላጎት ጋር በማጣጣም ሰልጣኞችንም ሆነ መንግሥትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ማሻሻያዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በግዛቸው ግርማዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.