ሻምፒዮኑ ሲዳማ ቡና ባሕር ዳር ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ባሕር ዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሀብታሙ ታደሰ አስቆጥሯል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል በተመሳሳይ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀዋሳ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ደግሞ ሸገር ከተማ ከመቻል ይገናኛሉ፡፡