Fana: At a Speed of Life!

መቐለ 70 እንደርታ እና ድሬዳዋ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 38ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ ነገሌ አርሲን 3 ለ 0 አሸንፏል።

በዛሬው ዕለት ቀን 9 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ የመቐለ 70 እንደርታን ግቦች መሃሪ አምሃ፣ ብርሃኑ አዳሙ እና ፍሬዘር ካሳ አስቆጥረዋል።

እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በጨዋታው የድሬዳዋ ከተማን ግቦች አስራት ቱንጆ እና አብዲሳ ጀማል ሲያስቆጥሩ፤ የአርባ ምንጭ ከተማን ብቸኛ ግብ መሪሁን መስቀለ ከመረብ አገናኝቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.