Fana: At a Speed of Life!

ለ10 ቀናት የሚቆየው 3ኛው የቴክኖ ኢትዮጵያ የፎቶ ኤግዚቢሽን…

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ቴክኖ ኢትዮጵያ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ ረገድ በትብብር መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ለ10 ቀናት የሚቆየው 3ኛው የቴክኖ ኢትዮጵያ የፎቶ ኤግዚቢሽን ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ከቦርድ ሴል ፎን አዲስ አበባ ጋር በመሆን በሕጻናት እና ወጣቶች የቴአትር ኮምፕሌክስ በድምቀት ተከፍቷል፡፡

የቴክኖ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽንና ከቦርድ ሴል ፎን አዲስ አበባ እንዲሁም ከሕጻናት እና ወጣቶች የቴአትር ኮምፕሌክስ ጋር በመተባበር ነው የCAMON 50 ስልክ ማስተዋወቂያና 3ኛውን የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን በድምቀት የከፈተው፡፡

በኤግዚቢሽኑ የቴክኖን አዲሱን ካሞን 50 ፕሮ ስልኮች በመጠቀም የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል የቱሪዝም መዳረሻዎች ተፈጥሮዎች ታሪኮች እና ሌሎች እይታዎች የተካተቱባቸው 100 ፎቶዎች ለዕይታ በቅተዋል፡፡

የዘንድሮውን ኤግዚቢሽን ለየት የሚያደርገው ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ጋር ቴክኖ አትዮጵያ አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት በኤግዚቢሽኑ መክፈቻ ቀን መፈራረሙ ነው፡፡

ይህም ሁለቱ ተቋማት በተለይም ቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ ሴክተሮች ላይ አብረው በጥምረት መስራት የሚያስችላቸውን ዕድሎች እንደሚፈጥር ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ማሕበረሰቡ ሀገሩን የማየት ልምዱን ከፍ ከማድረጉ ባሻገር የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችንም በሀገር እና ከሀገር ውጪ በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ የመንግሥት ሃላፊዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ፎቶግራፈሮች እና ሌሎችም የተገኙ ሲሆን÷ እጅግ ፈጠራ የታከለባቸው ምስሎች የተነሱበትን ቦታ የሚወክሉ የአርት ሥራዎችም ለዕይታ መቅረባቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡፡

ቴክኖ ካሞን 50 አጅግ ከፍ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን አካትቶ በኤ አይ ቴክኖሎጂ ፎቶዎችን ከፍ ባለ ደረጃ ኤዲት ማድረግ እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎችን መስራት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.