Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሚዛን አማን የቅደመ ምረቃ በረራ ጀመረ

‎አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሚዛን አማን ከተማ የሚያደርገውን የቅደመ ምረቃ በረራ በዛሬው ዕለት ጀምሯል።

‎‎በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ኤርፖርቶች ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጌታነህ አደራ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግሥት ዋና ተጠሪ ፍቅሬ አማን እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

አየር መንገዱ ወደ ሚዛን አማን ከተማ በሳምንት ሦስት ቀናት በረራ የሚያደርግ ሲሆን÷ ይህም ለማሕበረሰቡ ፈጣን፣ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ማቅረብ ያስችላል።

ሀገር ውስጥ የበረራ አድማሱን እያሰፋ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

‎በፍሬው አለማየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.