የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል።
በጉባዔው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የምክር ቤት ዓባላት፣ የክልሉ አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በጉባዔው የመስተዳድር ምክር ቤቱ የ2018 አፈጻጸም፣ የ2019 ጠቋሚ ዕቅድ፣ የም/ቤቱ አፈጻጸም እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ የጸረ ሙስና ኮሚሽንና የዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ሪፖርት ይቀርባል።
በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተመላክቷል፡፡