Fana: At a Speed of Life!

በ2018 በጀት ዓመት ከማዕድን ምርት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2018 በጀት ዓመት ከማዕድን ምርት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል አለ የማዕድን ሚኒስቴር፡፡
ሚኒስቴሩ በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እንዲሁም በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው።
የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በበጀት አመቱ 44 ነጥብ 067 ቶን ወርቅ ማምረት ተችሏል፡፡
ከዚህ ውስጥ 40 ነጥብ 86 ቶን ያህሉ በባህላዊ ማዕድን አምራቾች የተመረተ ሲሆን፥ ቀሪው 3 ነጥብ 209 ቶን ወርቅ ደግሞ በኩባንያዎች መመረቱን ጠቁመዋል።
በዚህም ከወርቅ ምርት ከ5 ነጥብ 65 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ነው የገለጹት፡፡
በአጠቃላይ ከማዕድን ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል ያሉት ሚኒስትሩ፥ በተያዘው የ2019 በጀት አመት 6 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን አመልክተዋል፡፡
በጀማል አህመድ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.