Fana: At a Speed of Life!

በሃይማኖት ጉዳዮችና በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ተመካካሪዎች መግባባት ላይ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሃይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሃሳቦቻቸው መግባባት ላይ ደርሰዋል አለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፡፡
ኮሚሽኑ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እያካሄደ ባለው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ በኮሚሽኑ ምክር ቤት በተለዩ ስምንት አጀንዳዎች ላይ ምክክር እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
አጀንዳዎቹ 500 አባላት ባሏቸው 8 የሥራ ቡድኖች ምክክር እየተደረገባቸው ሲሆን ÷ በኮሚሽኑ የአሰራር ሥነ ዘዴ መሰረት 500 አባላት ያሉት አንድ ቡድን በአንድ አጀንዳ ላይ እየተመካካረ ይገኛል፡፡
በዚህም በሃይማኖት ጉዳዮችና በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሲመካካሩ የቆዩት ሁለት ቡድኖች ዛሬ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጠናቀሩ ምክረ ሃሳቦቻቸው ላይ ተስማማተው በተዘጋጀው ቃለ ጉባዔ ላይ ተፈራርመዋል፡፡
የሌሎች አጀንዳዎች ተመካካሪዎችም በቀጣይ ቀናት በተመሳሳይ መልኩ የአጀንዳ ሃሳቦቻቸውን የጋራ አድርገው በቃለ ጉባዔዎቻቸው ላይ በመፈራረም ይስማማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኮሚሽኑ መረጃ አመልክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.