በመኸር እርሻ ከ17 ነጥብ 6 ሚሊየን ሔክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፈነ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመኸር እርሻ እስካሁን ከ17 ነጥብ 6 ሚሊየን ሔክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል አለ የግብርና ሚኒስቴር፡፡
ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል እንደገለጸው ÷ ከዘንድሮ የመኸር ወቅት እርሻ ከ729 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
ለዚህም በመኸር ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ 22 ሚሊየን 366 ሺህ 459 ሔክታር መሬት ለማልማት እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክቷል፡፡
እስካሁን ባለው የእርሻ እንቅስቃሴ 20 ሚሊየን 479 ሺህ 413 ሔክታር መሬት ታርሶ 17 ሚሊየን 658 ሺህ 586 ሔክታር በዘር መሸፈኑን አስታውቋል፡፡
በ2018/19 ምርት ዘመን በኩታ ገጠም እርሻ 16 ሚሊየን 4 ሺህ 527 ሔክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እስካሁን 9 ሚሊየን 753 ሺህ 728 ሔክታር በዘር መሸፈኑንም ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡
በመላኩ ገድፍ